
ደብረ ብርሃን: ጥር 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች በደብረ ብርሃን ከተማ ትጥቃቸውን ፈተው ወደ ሰላም መጥተዋል።
በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የክልል እና የዞን ከፍተኛ መሪዎች፣ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት ትጥቃቸውን በማስረከብ ወደሰላማዊ ኑሮ ተመልሰዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
