“ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ጉዟችን ተጠናክሮ ይቀጥላል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

8

ባሕር ዳር: ጥር 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አየር መንገዳችን ለ80 ዓመታት የዘለቀውን የአፍሪካ አስተሣሣሪነቱን የሚያጸና አዲስ ምዕራፍ ጀምሯል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በጉባ ካበሠሯቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች አንዱ የኾነውንና በአፍሪካ ግዙፉን የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ዛሬ በቢሾፍቱ አስጀምረናል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከስምንት ዐሥርት ዓመታት በፊት በጥቂት አውሮፕላኖች ጉዞውን ጀመረ። ዓላማው ኢትዮጵያን ከዓለም ጋር ማገናኘት ብቻ አልነበረም፤ የአፍሪካን ክብር በሰማይ ላይ ከፍ አድርጎ ማሳየት ጭምር እንጂ ብለዋል።

በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ ዐቅም የሚፈጥረው አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ፣ የኩራት ታሪካችንን ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር የኢትዮጵያ ግልጽ ራዕይና የብልጽግና ጉዞ ማሳያ ነው።

ፕሮጀክቱ የመንግሥታችንን በትልቁ አስቦ በትልቁ የማሳካት ዕይታን የሚገልጥ፣ የአፍሪካን የልዕልና ጉዞ በማረጋገጥ በዓለም አቪዬሽን መሪ ሚና እንዲኖራት የሚያስችል ነው።

የአየር መንገዳችንን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ይበልጥ ከፍ የሚያደርገው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፋይዳው የላቀ ነው። አየር መንገዳችን ወደ አፍሪካ መግቢያ እና መውጫ ዋናው በር ሆኖ ይቀጥላል ነው ያሉት።

ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ የፈጠራና ፍጥነት ጉዟችን በሁሉም ዘርፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮጵያ እምቅ አቅሟን እና ታላቅ ርዕይዋን የሚመጥን ሌላ ተጨማሪ ሜጋ ፕሮጀክት ጀምራለች።
Next articleየደን ጭፍጨፋ ሳይፈፀም መከላከል እና ጥፋት ሲፈፀምም መጠየቅ ይገባል።