ኢትዮጵያ ባሻሻለችው የጤና ፖሊሲ በርካታ ስኬቶች እየተመዘገቡ ነው።

11

አዲስ አበባ: ጥር 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጤና ሚኒስቴር የመጀመሪያውን የጤና ቁጥጥር ሥርዓት ጉባዔ እያካሄደ ነው።

ጉባዔው “ጠንካራ የጤና ቁጥጥር ለማይበገር ሥርዓት” በሚል መሪ መልዕክት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታዋ ፍሬሕይዎት አበበ ኢትዮጵያ ባሻሻለችው የጤና ፖሊሲ በርካታ ስኬቶች እየተመዘገቡ ነው ብለዋል።

ፓሊሲውን መነሻ በማድረግ ለጤና ኢንቨስትመንት በተሰጠው ልዩ ትኩረት ስምንት በመቶ የነበረው የሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርታማነት ባለፉት ሁለት ዓመታት ወደ 60 በመቶ ማደጉን ተናግረዋል።

ሜዲካል ቱሪዝምን ለማሳደግ እና ጥራት ያላቸው በሀገር ውስጥ ማከም የሚችሉ የጤና ተቋማትን ለመጨመር ስትራቴጂ ተቀርጾ እየተሠራ ባለው ሥራ አበረታች ውጤቶች እየታዩ መኾኑን ገልጸዋል።

የጤና ሥርዓቱን ፈዋሽ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ በሀገር ደረጃ ጠንካራ የቁጥጥር ሥርዓት ተግባራዊ መደረጉም ሀገሪቱ የዓለም ጤና ድርጅት እውቅናን አስገኝቶላታል ነው ያሉት።

ደኅንነቱ የተጠበቀ ጠንካራ የቁጥጥር ሥርዓት በመገንባት ፈዋሽ የምግብ እና የመድኃኒት ሥርዓት ከመገንባት አንጻር እየተመዘገቡ ያሉ ስኬቶችን ይበልጥ ለማጠናከር ጉባዔው መዘጋጀቱንም ገልጸዋል።

ጠንካራ ተቋማትን ለመፍጠር በትብብር እና በቅንጅት መሥራት እንደሚያስፈልግም አንስተዋል።

ዘጋቢ:- ኢብራሒም ሙሐመድ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከንግድ ባንክ ጋር የብድር አቅርቦት ስመምነት መደረሱ ለአርሶ አደሮች ትልቅ አቅም ይፈጥራል።
Next article“ሕዝቡ የሚፈልገው ሰላምን፣ አብሮነትን፣ አንድነትን እና ኢትዮጵያዊነትን ነው” አቶ ይርጋ ሲሳይ