የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ የአፈር ለምነትን ጨምሯል።

7
ጎንደር: ጥር 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የ2018 ዓ.ም የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማንጠርኖ ቀበሌ አስጀምሯል።
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በሚገኙ 15 ወረዳዎች የአፈር እና ውኃ ጥበቃ ሥራ በ889 ተፋሰሶች ላይ እንደሚከናወን ተገልጿል።
በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራው ሲሳተፋ ያገኘናቸው በጎንደር ዙሪያ ወረዳ የማንጠርኖ ቀበሌ ነዋሪዎች በየዓመቱ በሠሯቸው ተግባራት የአፈር ለምነትን መጨመር እንዳስቻላቸው ተናግረዋል። ከአካባቢው ሸሽተው የነበሩ የዱር እንስሳት መመለሳቸውንም ጠቅሰዋል።
ነዋሪዎቹ ለቤት እንስሳት ተጨማሪ መኖ ማግኘታቸውን እና ምንጮች መጎልበታቸውንም ተናግረዋል።
በሠሩት ሥራ ለውጥ ማግኘታቸውን የጠቀሱት ነዋሪዎቹ በቀጣይም የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቅሰዋል።
በዚህ ዓመት በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራው 52ሽህ ሄክታር መሬት እንደሚለማ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ ንጉሤ ማለደ ገልጸዋል።
የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራው ከመጀመሩ በፊት የተፋሰስ ልየታ፣ የሚሠራ የሰው ኀይል መለየት እና የቀያሽ አርሶ አደሮችን ወደ ሥራ የማስገባት ተግባር ሲከናወን መቆየቱን ጠቅሰዋል።
አርሶአደሮች የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ ያለውን ጠቀሜታ በመረዳት ባለቤት ኾነው በየዓመቱ ሥራውን እያከናወኑ መኾናቸውን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ አላምረው አበራ ተናግረዋል።
የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።
ዘጋቢ:- ዳንኤል ወርቄ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleግጭትን አውግዘዋል፤ ለሰላም ተነስተዋል!
Next articleየአፈር እና ውኃ ጥበቃ ሥራ በመሥራት ተፈጥሮን ከጉስቁልና መታደግ ይገባል።