
ባሕር ዳር: ጥር 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ)በደቡብ ጎንደር ዞን ላይ ጋይንት ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገብተዋል።
የሰላም አማራጭን የተቀበሉት ታጣቂዎች በወረዳው ወለላ ባሕር ቀጣና ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው። በአካባቢው በጫካ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ መግባታቸውን ቀጥለዋል።
ከላይ ጋይንት ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የሰላም አማራጭን የተቀበሉትን ታጣቂዎች በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሀገር መከላከያ ሠራዊት መሪዎች እና የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
