
ደሴ: ታኅሣሥ 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ዲ ኤም ቪ ፎር ደሴ የበጎ አድራጎት ድርጅት የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በማስመልከት ለ400 የከተማዋ አቅመ ደካማ ነዋሪዎች ማዕድ አጋርቷል።
የዲ ኤም ቪ ፎር ደሴ አማካሪ ማዘንጊያ አበበ በዓሉን በማስመልከት ነዋሪነታቸውን በአሜሪካ ካደረጉ የደሴ ከተማ ተወላጆች በተገኘ ከ450 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ለአረጋውያን፣ ለአካል ጉዳተኞች እና አቅመ ደካሞች ማዕድ ማጋራታቸውን ገልጸዋል።
የደሴ ከተማ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ ምሳዬ ከድር መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ካልኾኑ ተቋማት ጋር በመሥራት ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች አስፈላጊው እገዛ እየተደረገ መኾኑን ነው የተናገሩት።
አሚኮ ያነጋገራቸው አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች ለተደረገላቸው ድጋፍ አመሥግነዋል።
የበጎ አድራጎት ድርጅቱ በየጊዜው እገዛ እንሚያደርግላቸውም ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ሠልሀዲን ሠይድ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
