ሦስቱ ሀገራት ልዩነታቸውን በውይይት እንዲፈቱ የአፍሪካ ኅብረት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ሙሳ ፋኪ መህማት አስታውቀዋል፡፡

164

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 19/2012 ዓ.ም (አብመድ) የኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ጋር ትናንት በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡

ኢትየጵያ፣ ግብጽና ሱዳን ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር በተያያዘ እስከዛሬ ድረስ ያደረጓቸውን ውይይቶች እና የኢትዮጵያን አቋም በተመለከተ አቶ ገዱ ለሙሳ ፋኪ ማህመት አስረድተዋቸዋል፡፡

ከአባይ ውሀ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ባልተሳተፈችባቸው የተፈረሙ የቅኝ ግዛት ውሎችን እንደማትቀበልም ሚኒስትሩ ገልጸውላቸዋል፡፡ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሀ ሙሊትን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ለማከናወን አስፈላጊው ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም አቶ ገዱ አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን በመጠቀም ልማቷን የማፋጠን ህጋዊ እና ተፈጥሯዊ መብቷ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ የአፍሪካ ኅብረትም በመርህ ላይ የተመሠረተ ድጋፉን ሊያደርግ እንደሚገባ ሚኒስትሩ መጠየቃቸው ታውቋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት በበኩላቸው ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎች እንደሚያስፈልጋቸው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

የአፍሪካ ኅብረት በዚህ በኩል ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ ማሳወቃቸውንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ኅብረቱ ሦስቱ ሀገራት ተቀራርበው ልዩነታቸውን በውይይት እንዲፈቱ የውይይት መድረኮችን ለማመቻቸት እንደሚንቀሳቀስም ሙሳ ፋኪ ማህማት ገልጸዋል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleበሦስት ወራት ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ180 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል፡፡
Next articleስድስት ዩኒቨርስቲዎች የጉና ተራራ አከባቢን ለማልማት ስምምነት ተፈራረሙ፡፡