
ባሕርዳር፡ ታኅሣሥ 28/2018 (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገብተዋል።
የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች የበደሉትን ሕዝብ በመካስ ሰላማዊ ሕይወት ለመምራት መወሰናቸውን ተናግረዋል። ሌሎች በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎች ወጣትነታቸውን ለልማት እና ሰላም ግንባታ በማዋል የበደሉትን ሕዝብ መካስ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የሰላምን መንገድ መምረጥ አዋጭ ነው ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
