
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋርተዋል።
አመራርነት በፓሊሲና እና በተቋማት ብቻ ሳይኾን በሰብአዊ ግንኙነቶችም ጭምር ይከናወናል።
ዛሬ በመላው ሀገራችን ቤተሰቦች የልደት በዓልን ለማክበር በሚሰናዱበት ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ጋር በመኾን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከሚገኙ ሠራተኞች መሀል ተገኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁልጊዜም በበዓላት ጊዜ እንደሚያደርጉት አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሠራተኞች እና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤቱ ለሚደግፋቸውና ለሚያሳድጋቸው ሕፃናት የበዓል ስጦታዎችን ሰጥተዋል። መዓድም አጋርተዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ይኽም በየዕለቱ አስተዋጽኦዋቸው ጎልቶ ባይነገርም ለሀገር የሚያገልግሉ ሠራተኞችን እውቅና የሠጠ፣ ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናትም በማኅበረሰባችን ስፍራ እንዳላቸው የሚያሳይ ፍቅርን ያካፈለ ተግባር ነበር።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
