
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምክር ቤቱ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል።
ባካሄደው መደበኛ ስብሰባም ወይዘሮ ሃይማኖት ዘለቀን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ የቀረበውን ረቂቅ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
ወይዘሮ ኃይማኖት ዘለቀ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከዘጋቢነት እስከ አርታኢነት እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በሙያቸው አገልግለዋል፡፡
በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ጽሕፈት ቤት በምክትል ቢሮ ኅላፊ ማዕረግ የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ኅላፊ በመሆን ማገልገላቸው ተገልጿል፡፡
በቀድሞ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት መሥራታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
