“የመንገድ መሠረተ ልማት የኢኮኖሚ ዕድገት ጉዟችን ቁልፍ ጉዳይ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

13

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የሚኤሶ – ድሬዳዋ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት የሥራ ሂደትን በተመለከተ ከሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የመንገድ መሠረተ ልማት የኢኮኖሚ ዕድገት ጉዟችን ቁልፍ ጉዳይ ነው ብለዋል።

ዛሬ የሚኤሶ – ድሬዳዋ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት የሚገኝበትን የሥራ ሂደት በተመለከተ ከሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂደናል ነው ያሉት።

በፕሮጀክቱ የሥራ ሂደት እየተከናወኑ የሚገኙ የሰው ኃይል ዝግጅት፣ የማሽነሪና ሌሎች የግንባታ ዕቃዎች አቅርቦት፣ የመስክ ዝግጅት እና ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር የተደረጉ ውይይቶች ምን ይመስላሉ የሚሉትን አይተናል ብለዋል።

የሚኤሶ – ድሬዳዋ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት ለከባድ የጭነት መኪኖች አዳጋች የነበረውን መንገድ ምቹ በማድረግ፣ የወጪና ገቢ ንግዳችንን ያቀላጥፋል፤ በቀጣናዊ ትስስር ረገድ ያለንን ሚናም ያጎለብታል ነው ያሉት።

ፕሮጀክቱ የኢኮኖሚያችንን ተወዳዳሪነትና የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል ጉልህ አበርክቶ የሚኖረው በመኾኑ በተያዘለት እቅድ መሠረት እንዲጠናቀቅ የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ ይገባል ብለዋል በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የምናደርገው ርብርብ ሰፊ ትኩረት የሚሰጠው ይኾናል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next articleበሥልጠና ያገኙትን አቅም በመጠቀም ሰላምን ለማጽናት እንደሚሠሩ ተመራቂ የሰላም አስከባሪ አባላት ተናገሩ።