ኢትዮ ቴሌኮም ለባለ ዕድለኞች የመኪና ሽልማቱን አስረከበ።

22

አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮ ቴሌኮም በ131 ዓመት የአብሮነት ጉዞ ውስጥ ኢትዮ ቴሌኮም ሜጋ ፕሮሞ 130 በሚል 3ኛው የሽልማት ሥነ ሥርዓት አካሂዷል።

ኩባንያው 130ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከመስከረም 12/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለደንበኞች ባዘጋጀው የኢትዮ 130 ሜጋ ፕሮሞ እና ኢትዮ 131 ላኪ ስሎት ሽልማት መርሐ ግብር ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ሲያበረክት መቆየቱን የሽያጭ ቺፍ ኦፊሰሩ መሐመድ ሐጂ ተናግረዋል፡፡

ዛሬም ዕጣ ለወጣላቸው የአዲስ አበባ እና የጅማ ባለዕድሎች ሁለት ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ቃል በገባው መሠረት ቁልፍ አስረክቧል ነው ያሉት።

ኩባንያው በ65 ሳምንታት ውስጥ አራት የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለአዲስ አበባ፣ አዳማ እና ወሊሶ ባለዕድሎች፤ 13 ባለሦሥት እግር ተሽከርካሪዎችን ለአርባምንጭ፣ ሀረር፣ አርሲ ነገሌ፣ አዲስ አበባ፣ ሆሳዕና፣ አዳማ፣ ሀዋሳ፣ ወልቂጤ እና ቦንጋ ባለዕድለኛ ደንበኞቹ ቁልፍ ማስረከቡን አንስተዋል።

በተጨማሪም 372 ዘመናዊ ስማርት ስልኮችን፣ ለ2ሺህ 59 ደንበኞች በየቀኑ እና በየሳምንቱ በድምሩ 40 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የቴሌብር ኤሌክትሮኒክስ ገንዘብ፣ ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ የሞባይል ጥቅሎችን ጨምሮ፤ ከ127 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ አጠቃላይ ዋጋ ያላቸውን ሽልማቶች አበርክቷል ብለዋል።

ዛሬ የመጨረሻዎቹን ስድስት ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖች ዕጣ የማውጣት መርሐ ግብር የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ መሪዎች፣ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ተወካዮች፣ የሚዲያ አጋሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተከናውኗል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ሽልማቶች ወደ 43 ከተሞች መዳረሳቸውም ተገልጿል። ሽልማቶቹን የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ቴክኖሎጂ ኦፊሰር ታሪኩ ደምሴ አስረክበዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በቀጣይም ቴሌ ፕሌይ የሚል ሽልማት ይዞ እንደሚመጣ ይፋ ተደርጓል።

ዘጋቢ፦ድልነሳ መንግሥቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት አባላትን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሠራ ነው።
Next articleየበዓል ገበያ በፍኖተሰላም ከተማ