
ጎንደር: ታኅሣሥ 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በ13ኛው ዙር የበሽ ጥቅል ሽልማት በጎንደር ከተማ እድለኛ ለኾኑት ወይዘሮ ያለምወርቅ አበበ ሽልማታቸውን አስረክቧል።
የአንድ ሚሊዮን ብር ተሸላሚዋ ያለምወርቅ አበበ
ሳፋሪኮም የበሽ ጥቅልን በመጠቀም በደረሳቸው የበሽ ጥቅል ዕጣ መሠረት የአንድ ሚሊዮን ብር ዕድለኛ መኾናቸውን ተናግረዋል። በሽልማቱም ደስተኛ መኾናቸውን ገልጸዋል።
በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሰሜን ምሥራቅ እና የሰሜን ምዕራብ የውጭ ግንኙነት ክፍል ኀላፊ ጥላሁን ብርሃኑ ሳፋሪኮም በበሽ ጥቅል በርካቶችን ሚሊየነር እያደረገ መኾኑን ተናግረዋል።
ዛሬም በጎንደር ከተማ በ13ኛው ዙር የአንድ ሚሊዮን ብር የተሸለሙት ዕድለኛ 32ኛዋ የበሽ ጥቅል ተሸላሚ መኾናቸውን ገልጸዋል።
የበሽ ጥቅል በቀጣይም ሌሎች ዕድለኞችን ሚሊየነር የማድረግ ጉዞውን ይቀጥላል ያሉት አቶ ጥላሁን ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከቴሌኮም አገልግሎት በተጨማሪ በ”ኤምፔሳ” የፋይናንስ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ አመላክተዋል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የትምህርት ተቋማት ዲጂታል አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲኾኑ ለማስቻል እና በሌሎችም ማኅበራዊ አገልገሎት ውስጥ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነውም ብለዋል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ተደራሽ መኾኑን አንስተዋል። ተቋሙ ለበርካቶች ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉንም አስረድተዋል።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ በላይነህ ይደግ እንዲህ አይነት ተግባራት ለወጣቶች የሥራ ዕድልን መፍጠርን ጨምሮ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለመፍጠር የሚያስችሉ መኾናቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ ቃልኪዳን ኃይሌ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
