በትራፊክ አደጋ ምክንያት እየገጠመ ያለውን ማኅበራዊ ቀውስ ለመቀነስ እየተሠራ ነው።

6

ደብረብርሃን: ታኅሣሥ 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴራል መንገድ ደኅንነት እና መድን ፈንድ አገልግሎት የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የሚያስችል የምክክር እና የሥልጠና መድረክ በደብረብርሃን ከተማ እያካሄደ ነው።

የፌዴራል መንገድ ደኅንነት እና መድን ፈንድ አገልግሎት ምክትል ሥራ አሥፈፃሚ መሐመድ ሀሰን የትራፊክ አደጋ እንደ ሀገር ችግር ኾኗል ብለዋል።

ይህንን ችግርም ለመቀነስ እንደሀገር በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መኾናቸውን ገልጸዋል። በ10 ክልሎች እና በሁለት ከተማ አሥተዳደሮች በትምህርት ካሪኩለሙ ውስጥ ተካቶ እየተሠራበት መኾኑን ጠቅሰዋል። በትራፊክ አደጋ ምክንያት እየገጠመ ያለውን ማኅበራዊ ቀውስ ለመቀነስ እየተሠራ መኾኑንም አመላክተዋል።

የአማራ ክልል መንገድ፣ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ቢሮ ኀላፊ ጋሻው አወቀ (ዶ.ር) ሀገሪቱ በቁጥር ትንሽ ተሽከርካሪዎችን ይዛ በርካታ አደጋዎች የሚከሰቱባት መኾኗን ገልጸዋል። የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ነው ያሉት።

በትራፊክ አደጋ ምክንያት ከፍተኛ የንብረት ውድመት እና የሰው ሕይወት መጥፋት እንደሚያጋጥምም ተናግረዋል።

ዘጋቢ፦ ዮናስ ታደሰ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበላይ ጋይንት ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀበሉ።
Next articleግብይት በላሊበላ!