
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ)በደቡብ ጎንደር ዞን ላይ ጋይንት ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገብተዋል።
የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች የበደልነውን ሕዝብ ለመካስ የሰላም አማራጭን ተቀብለናል ብለዋል። በተሳሳተ መንገድ ጫካ በመግባት የሚኖሩበትን አካባቢ ሕዝብ ማበሳቆላቸውን እና መበደላቸዉን ገልጸዋል።
ታጣቂዎች የሰላም አማራጭ እንዲቀበሉ ያደረጉ የሃይማኖት አባቶች ሰላም የሁሉም ነገር መሠረት መኾኑን ተናግረዋል። ታጣቂዎች የሃይማኖት አባቶችን እና የሀገር ሽማግሌዎችን ምክር በመስማታቸው ምስጋና ይገባቸዋል ነው ያሉት።
በአካባቢዉ የሚንቀሳቀሰው የሀገር መከላከያ የአንድ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል አሰጋ አከለ የታጠቁ ኃይሎች የተሰለፉበት ዓላማ የተሳሳተ መኾኑን ተረድተዉ መግሥት የአቀረበዉን የሰላም አማራጭ በመቀበላቸዉ አመስግነዋል።
ሌሎች ታጣቂዎችም የቀረበውን የሰላምን አማራጭ በመቀበል በሰላም እንዲገቡ ጥሪ አቅርበዋል።
የላይ ጋይንት ወረዳ ሰላም እና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አገኘው አራጌ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች በአካባቢያቸዉ ሰላም እንዲሰፍን እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ የሚመሰገን ተግባር ነዉ ብለዋል።
ወረዳው በተደጋጋሚ በተካሄዱ ግጭቶች ኢኮኖሚያዊ እና ሰበዓዊ ጉዳቶች እንደደረሱበት ተናግረዋል።
ከላይ ጋይንት ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው አሁን ላይ የሚያስፈልገው ግጭት ሳይኾን ሰላም እና ልማት ሊኾን እንደሚገባም አመላክተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
