አዋሽ ባንክ በደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ አረጋውያን እና አቅመ ደካማ ወገኖች 900 ሺህ ብር የሚገመት የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ።

9

 

ደብረ ብርሃን: ታኅሣሥ 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአዋሽ ባንክ ሰሜን አዲስ አበባ ቀጣና ዳይሬክተር ታዬ አበበ ባንኩ ከሚሰጠው መደበኛ አገልግሎት በተጨማሪ በሚሠራቸው የማኅበረሰብ አገልግሎት ተግባራት የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።

ድጋፉም ለ100 ሰዎች ተደራሽ ኾኗል። ለእያንዳንዳቸው 25 ኪሎ ግራም የዳቦ ዱቄት፣ 5 ሊትር ዘይት እና 3 ሺህ ብር ጥሬ ገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

“ክብራችን ወገናችን፣ ደስታችን ማካፈላችን” በሚል መሪ መልዕክት እየተደረገ የሚገኘው ድጋፍ ሌሎች አካባቢዎችንም ተደራሽ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ባንኩ በጥቅሉ በዚህ ዙር በሚያደርገው እገዛ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ድጋፎችን ተደራሽ እንደሚደረግ ነው የተገለጸው።

ድጋፍ የተደረገላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችም ባንኩ ላደረገለቸው እገዛ አመስግነዋል፡፡

ዘጋቢ:- ገንዘብ ታደሰ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከደባርቅ-በለስ- መካነ ብርሃን ድረስ የሚገነባው የመንገድ ሥራ ምን ላይ ደረሰ
Next articleየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ከ2 ትረሊዮን ብር በላይ ኾኗል።