
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ጥናታዊ ጽሑፍ እያቀረቡ ነው።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ተማሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) “የምሁራን ሚና ለሀገራዊ ብልጽግና” በሚል ርዕስ የጥናታዊ ጽሁፍ እያቀረቡ ይገኛሉ።
የአካዳሚያዊ መሪዎች እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ገለጻው እየተሰጠ ይገኛል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የዛሬው መርሐ ግብር 75ኛ ዓመት በዓሉን ለማክበር ላለፉት ሳምንታት ሲደረጉ የነበሩ ተከታታይ ገለጻዎች እና ፕሮግራሞች ማጠቃለያ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
