ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ እና ለኢንዱስትሪ ምርቶች የገበያ ትስስር ለመፍጠር እየተሠራ ነው።

17
ገንዳ ውኃ: ታኅሣሥ 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎንደር ዞን በ2017/18 ዓ.ም የምርት ዘመን ከ525 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታውቋል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት እና ጥበቃ ባለሙያ ጌትነት ካሣሁን በዘር ከተሸፈነው መሬት ከ9 ሚሊዮን 69 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።
በዘር ከተሸፈነው ውስጥ ከ220 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በኩታገጠም አስተራረስ በአኩሪ አተር፣ በሰሊጥ እና በማሽላ ዘር መሸፈኑን ተናግረዋል።
ከባለፈው ዓመት የምርት ዘመን ጋር ሲነፃፀር የዚህ ዓመቱ ምርት የተሻለ መኾኑንም ጠቁመዋል።
በዞኑ ከ210 በላይ ሁለገብ መውቂያዎችን ሥራ ላይ በማሰማራት ምርትን መሰብሰብ ተችሏል ነው ያሉት።
ከመውቂያዎች በተጨማሪ በብዛት የጉልበት ሠራተኞችን ወደ ዞኑ በማስገባት ምርቶች በወቅቱ እንዲሰበሰቡ ተደርጓል ብለዋል።
ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ እና ለኢንዱስትሪ ምርቶች የገበያ ትስስር ለመፍጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመኾን ሥራዎች እየተሠሩ መኾናቸውን አስረድተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየኮሪደር ልማት ወልድያን አስውቧታል።
Next articleየክልል እና የፌዴራል መንግሥት መሪዎች በባሕር ዳር ከተማ የኢንዱስትሪ ቦታዎችን እየጎበኙ ነው።