የጤና መድኅን አገልግሎትን ማስፋት ሕይዎትን መታደግ ነው።

5
ደብረ ታቦር: ታኅሣሥ 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አገልግሎት ሕይዎትን እየታደገ መኾኑን አሚኮ ያነጋገራቸው የደብረ ታቦር ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ሀሳባቸውን ያጋሩን የከተማው ነዋሪ ገሰሰ አዲስ የጤና መድኅን አገልግሎት ተጠቃሚ ባልነበሩበት ወቅት ለሕክምና ከፍተኛ ወጭ ያወጡ እንደነበር አስታውሰዋል።
የጤና መድኅን ተጠቃሚ በመኾናቸው በፊት ይገጥማቸው የነበረውን ችግር እንዳስቀረላቸውም ነው የገለጹልን። “የኅብረተሰብ ጤና መድኅን አገልግሎትን ማስፋት ሕይዎትን መታደግ ነው” ያሉት ደግሞ ሌላኛዋ ተጠቃሚ ወይዘሮ ትሁኔ ካሴ ናቸው። ይሁን እንጅ ክፍያው ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍል ያማከለ እና ተመጣጣኝ ቢኾን መልካም ነው ብለዋል።
የደብረ ታቦር ልዑል ዓለማየሁ ጤና ጣቢያ ኀላፊ መንበር ብርሃን የማኅበረሰቡ የጤና መድኅን አገልግሎትን የመጠቀም ግንዛቤው ማደጉን ተናግረዋል።
የጤና መድኅን አገልግሎት መጠቀም ከሁሉም በላይ ጥቅሙ ለራስ ነው ያሉት ኀላፊው ሁሉም ማኅበረሰብ የጤና መድኅን አባል በመኾን እና የአባልነቱን ደብተር በመያዝ ተጠቃሚ ሊኾን ይገባል ብለዋል።
የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ ኀላፊ በረከት ገደፋው የኅብረተሰብ ጤና መድኅን አገልግሎትን ለማስፋት ንቅናቄ መጀመሩን ገልጸዋል።
ለማከናወን ከታቀደው ውስጥ 85 በመቶ በላይ ያህሉን መፈጸም እንደተቻለም ተናግረዋል። የአገልግሎት ክፍያው ሁሉንም ማኅበረሰብ ያማከለ መኾኑን የገለጹት ኀላፊው በፊት ከነበረው ክፍያ ጋር ሲነጻጸር ግን የመድሃኒት ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት ልዩነት አለው ነው ያሉት።
ኅብረተሰቡ የሚከፍለው በቦርድ የተወሰነ እና ኪስን የማይጎዳ እንደኾነም ነው የተናገሩት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleያለ አግባብ የተመዘበረ ሃብትን በማስመለስ ረገድ በትኩረት መሥራቱን ፍትሕ ቢሮ አስታወቀ።
Next articleየኀይል መቆራረጥ በመቀረፉ የደብረ ታቦር የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ መሻሻል እያሳየ ነው።