
ደሴ: ታኅሣሥ 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ወሎ ዞን የሥራ ኀላፊዎች እና የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከአምባሰል ወረዳ ሕዝብ ጋር በወቅታዊ የሰላም እና የጸጥታ ጉዳይ በውጫሌ ከተማ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ የተገኙት የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሊ መኮንን ሕዝባችንን ለችግር የዳረገውን የጸጥታ ችግር በሰላም ለመፍታት መንግሥት እየሠራ ነው ብለዋል።
የጽንፈኛውን አላማ የተረዱ ወገኖች አሁን ላይ የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ በመኾኑ ማኅበረሰቡ በተሳሳተ መንገድ ላይ ያሉ ኀይሎችን መምከር እና ወደ ሰላም ማምጣት ይገባል ነው ያሉት።
አሁን ላይ የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ መከላከያ ሠራዊቱን እና የጸጥታ ኀይሉን በማገዝ አካባቢያችሁን መጠበቅ አለባችሁም ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ የኅብረተሰብ ክፍሎችም ባለፉት ሁለት ዓመታት በአካባቢያቸው ያለው የጸጥታ ኹኔታ ለችግር ዳርጓቸው መቆየቱን አንስተዋል። ሰላም ናፍቆናል፤ ተነጋግረን ችግሩን እንፍታ ሲሉም ተናግረዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
