
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎጃም ዞን በቡሬ ዙሪያ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።
የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች በተሳሳተ መንገድ ጫካ በመግባት በሕዝባቸው ላይ የሰላም እጦት እንዲፈጠር ምክንያት መኾናቸውን ገልጸዋል።
ሕዝባቸውን ለመካስ የቀረበውን የሰላም አማራጭ መቀበላቸውንም አመላክተዋል። ከቡሬ ዙሪያ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሕዝብን ለመካስ እና ለማገልገል መዘጋጀታቸውንም አመላክተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
