
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎጃም ዞን በጃቢ ጠህናን ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገብተዋል።
ታጣቂዎቹ የአማራን ሕዝብ ነጻ እናወጣለን በሚል ወደ ጫካ ገብተን በሕዝባችን ላይ የሰላም እጦት እንዲከሰት ምክንያት ኾነናል ብለዋል። የበደሉትን ሕዝብ ለመካስ እና ለማገልገል የሰላምን አማራጭ መቀበላቸውንም ገልጸዋል።
ከምዕራብ ጎጃም ዞን ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሌሎች ታጣቂዎችም የሰላም አማራጭ እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
