
ከሚሴ፡ ታኅሣሥ 21/2018ዓ.ም (አሚኮ) የከሚሴ ከተማ አሥተዳደር በወቅታዊ የሰላም እና የልማት ጉዳዮች ዙሪያ ከወጣቶች ጋር ተወያይቷል።
የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች በሀገረ መንግሥት እና በዴሞክራሲ ግንባታ ውስጥ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መኾኑን ገልጸዋል።
ወጣቶችን ያላሳተፈ የሰላም ግንባታ ሥራ ስኬታማ እንደማይኾንም ተናግረዋል። በወጣቶች አደረጃጀት በመደራጀትም የከተማቸውን ሰላም እያረጋገጡ መኾናቸውን ጠቁመዋል።
የወጣቶችን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥም የከተማው እና የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ተቀናጅተው ሊሠሩ ይገባልም ብለዋል።
የከሚሴ ከተማ አሥተዳደር ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አንሻ አሊ ከተማ አሥተዳደሩ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሠራ መኾኑን ገልጸዋል።
በከተማ አሥተዳደሩ የሚሠሩ ልማቶች ለወጣቶች የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።
በቀጣይም የወጣቶችን ልማት ለማረጋገጥ ታቅዶ እየተሠራ መኾኑን ጠቁመዋል።
የከሚሴ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሸሪፍ ቃሲም ወጣቶችን ያላሳተፈ የሰላም ግንባታ ሥራ እንደማይሳካ ገልጸዋል። ወጣቶችን በሰላም ግንባታ ሥራዎች እያሳተፉ መኾኑን ተናግረዋል።
የወጣቶችን የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ ከተማ አሥተዳደሩ ከወጣቶች ጋር ተቀራርቦ እየሠራ ነው ብለዋል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሴቶች ክንፍ ኀላፊዋ ፋጡማ የሱፍ የሴቶች እና የወጣቶችን አደረጃጀቶች እስከ ታች ድረስ ለማጠናከር በትኩረት እየተሠራ መኾኑን አስረድተዋል።
ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሂም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
