የአማራ ክልል የባሕል ፍርድ ቤቶች ዕውቅና መስጫ እና የሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

2
ባሕርዳር፡ ታኅሣሥ 21/2018ዓ.ም (አሚኮ)የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የባሕል ፍርድ ቤቶች ዕውቅና መስጫ እና የሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እያካሄደ ነው።
የባሕል ፍርድ ቤቶች በሽምግልና መሠረት ቁርሾን በማስቀረት እርቅ የሚያወርዱ የሕዝብ የሰላም እሴቶች ናቸው።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም የባሕል ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋም ረቂቅ አዋጅ አውጥቶ በክልሉ ምክር ቤት አስጸድቋል። ዛሬ ደግሞ የባሕል ፍርድ ቤቶችን የዕውቅና የመስጠት እና የሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እያካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ ላይ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ከየወረዳው የተወከሉ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፦ አሚናዳብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleታኅሣሥ 20/2018 ዓ.ም
Next articleበሀሰት መመስከር የሕግ ተጠያቂነቱ እስከምን ድረስ ይኾን?