ስታሸንፍ ተፈላጊ ትኾናለህ!

4
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 1896 ዓ.ም በዚህ ሳምንት ታኅሣሥ 15 የመጀመሪያውን የአሜሪካ ዲፕሎማቲክ ልዑክ ወደ ኢትዮጵያ መምጣትን ታሪክ ያወሳል።
በዚህ ጊዜ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ቴዎዶር ሮዝቬልት አምባሳደር ሮበርት ፒ ስኪነርን ወደ አዲስ አበባ የላኩት ከዳግማዊ አጼ ምኒልክ ጋር የንግድ ስምምነት ለመፈረም ነበር። ልዑኩ የመጣው ኢትዮጵያ በዓድዋ ጦርነት የጣሊያንን ወራሪ ኃይል ድል ባደረገችበት እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ስሟ በገነነበት ወሳኝ ወቅት ነበር።
የኢትዮጵያ ድል ለጥቁር አሜሪካውያን እና ለፓን-አፍሪካኒስት ንቅናቄ ትልቅ መነሳሳትን ፈጥሯል። ጥቁር አሜሪካውያን ጸሐፊዎች የኢትዮጵያ ድል የቅኝ ግዛትን ብቻ ሳይኾን ዘመናዊውን ዘረኝነት ድል ያደረገ እንደኾነ ይገልጹት ነበር።
የልዑኩ አባላት እና አብረዋቸው የነበሩ የባሕር ኃይል ወታደሮች ከአጼ ምኒልክ የክብር ሜዳሊያ ተሰጥቷቸዋል።
ሜዳሊያው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት ማለትም አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሪቫን እና የንጉሠ ነገሥቱ ምስል ያለበት የወርቅ ተንጠልጣይ ነበረው።
በጉዞው ወቅት በአዲስ አበባ፣ በሐረር እና በድሬዳዋ የተነሱ ከ150 በላይ ታሪካዊ ፎቶግራፎች ኦሃዮ በሚገኘው የማሲሎን ሙዚየም ተቀምጠው ይገኛሉ።
አርካይቭ ዶት ኦርግ እና ጀስት ቱር ድረ-ገጾችን በመረጃ ምንጭነት ተጠቅመናል።
👉 ባቡር የፈጠራት ከተማ
ድሬዳዋ የተመሠረተችው የመጀመሪያው ባቡር ከጅቡቲ ተነስቶ በዚህ ሳምንት ታኅሣሥ 14/1895 ዓ.ም ከተማዋ የገባ ዕለት ነበር።
ባቡሩ በሀረር በኩል እንዲያልፍ ታስቦ የነበረ ቢኾንም ድሬዳዋ ለባቡሩ የእንፋሎት ወይም ስቲም አስፈላጊ የኾነው የውኃ ክምችት ስላላት እና ሜዳማ በመኾኗ ተመርጣለች።
ከጅቡቲ እስከ አዲስ አበባ ባለው የሀዲድ መስመር ላይ የሚገኙት 35 ጣቢያዎች እንደ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ መተሀራ፣ ሞጆ መሰል ከተሞች እንዲመሠረቱ እና እንዲያድጉ ምክንያት ኾኗል።
ባቡሩ የሀገሪቱ የገቢ እና ወጭ ንግድ የጀርባ አጥንት ነበር። ለበርካታ ነዋሪዎችም የሥራ ዕድል ማለትም ለምግብ አቅራቢዎች፣ ለጭነት ሠራተኞች እና ለረዳቶች ፈጥሮ የነበረ ዘርፍም ነው።
ለባቡር ሠራተኞች መኖሪያ የሚኾን የ”ከዚራ” ሰፈር እንዲመሠረት እና ከ100 ዓመታት በላይ እያገለገለ ያለው “የፈረንሳይ ሆስፒታል” እንዲቋቋም ምክንያትም ኾኗል።
አዲስ ዘመን ጋዜጣን በመረጃ ምንጭነት ተጠቅመናል።
👉 የፕሬዝዳንቱ ደስታ
ኢትዮጵያ ባዘጋጀችው የምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ዚምባብዌን በፍጹም ቅጣት ምት በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን ከፍ ያደረገችበት ጊዜ በዚህ ሳምንት ታኅሣሥ 17/1980 ዓ.ም ነበር።
ዋንጫውን ለብሔራዊ ቡድኑ አምበል ገብረመድን ኃይሌ የሰጡት ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያም ነበሩ። በወቅቱ የፕሬዝዳንቱ ደስታ የተለየ እንደነበር ዘብላክ ላየን መጽሐፍ ላይ ተከትቦ ይገኛል።
በምሥጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየወልድያ ከተማን ዕድገት ለማሳለጥ የኅብረተሰቡ ትብብር እና ድጋፍ አስፈላጊ ነው።
Next article“በተሳሳተ ግንዛቤ ጫካ የወጣችሁ ታዳጊዎች እንደእኔ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ”