
ደብረማርቆስ፡ ታኅሣሥ 18/2018 ዓ.ም አሚኮ) በታጣቂ ቡድኑ ራሱን የቴዎድሮስ እዝ ብሎ የሚጠራው ቡድን የካርታ እና ምህንድስና ሠራተኛ ኾኖ ያገለግል የነበረው ሻምበል ይልቃል ታደለ መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ ገብቷል፡፡
በነበረው የሁለት ዓመት በላይ ቆይታ አጠቃላይ ትግሉ ዓላማ እንደሌለው መረዳት እንደቻለ ገልጿል።
ታጣቂ ቡድኑ የሕዝብን ጥያቄ ለማስመለስ ሳይኾን የግል ፍላጎቱን ለማሳካት የሚንቀሳቀስ በመኾኑ የሰላም አማራጭን መቀበል እንደቻለም ተናግሯል።
የሕዝቡን ሰቆቋ የጨመረው የትጥቅ ትግሉ የአማራ ሕዝብ ጥያቄን የሚፈታ ሳይኾን የግለሰቦች የሃብት ማካበቻ በመኾኑ ነው ብሏል።
በትጥቅ ትግሉ የትምህርት ተቋማት ወደ ሥራ እንዲገቡ ሃሳብ ሲነሳ መግባባት አልተቻለም ነው ያለው። ይህም ለብዙዎች ቅራኔ መንስኤ መኾኑንም አመላክቷል።
ያልተማሩ ቤተሰቦች አስተምረውኝ በማይኾን ትግል የማይማር ትውልድ ልፈጥር አይገባኝም ያለው ሻምበል ይልቃል ሕጻናት ወደ ትምህርት ገበታ ባለመመለሳቸው እና የትምህርት ተቋማት ለሌላ ዓላማ መዋላቸው ሁሌም የሚጸጽተው ጉዳይ መኾኑን ገልጿል።
በውጭ ሚዲያዎች በሚሰማው የተሳሳተ መረጃ ተነሳስቶ ወደ ትጥቅ ትግሉ መግባቱን የሚናገረው ሻምበል ይልቃል ትግሉን ሲቀላቀል ያገኜው ነገር ግን የተለየ እና የክልሉን ሕዝብ ለማያባራ ቀውስ እንደሚዳርግ መረዳቱን ተናግረዋል።
መንግሥት የሰላም ጥሪውን ተቀብለው የሚመጡትን ታጣቂዎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባውም አንስቷል።
ላልተፈለገ ዓላማ የሕይወት መሥዋትነት እየከፈሉ ያሉ የታጣቂ ቡድኑ አባላት የሕዝቡን ችግር እና ስቃይ ማራዘም የለባቸውም በሰላም ወደ ቀደመ ሕይወታቸው መመለስ ይገባቸዋል ብሏል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
