ኢንተርፕራይዞች የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ናቸው።

10

አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ባዛር በአዲስ አበባ ከተማ አስጀምሯል።

ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማነትን በማሳደግ ረገድ ተጨባጭ ሥራ እየተገበረች መኾኑን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን በጥራት በማምረት ለገበያ እንዲያቀርቡ፣ ወደ ውጭ በመላክም የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ግኝት በማሳደግ በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል እና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲፈጠር ለማድረግ ባዛሮች ትልቅ ሚና አላቸው።

አሚኮ ያነጋገራቸው “የድምቅ በሀገር ምርት” ባዘር ተሳታፊዎች እንዳሉት ይህ ዕድል መዘጋጀቱ የሥራ ዕድልን ከማስገኘት ባለፈ ሙያቸውን በማዳበር እና የተሻለ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሚናው ከፍ ያለ ነው ብለዋል። በተለይም የዕውቀት ሽግግር ለማድረግ ያለው አበርክቶ ከፍ ያለ እንደኾነም አመላክተዋል።

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዲኤታ ሰለሞን ሶካ “ድምቅ በሀገር ምርት” በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር እና በኔዘርላንድስ ልማት ድርጅት/SNV/ በጥምረት መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

እንደዚህ አይነት ባዛሮች መዘጋጀታቸው ወጣቶችን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት የጎላ ሚና አላቸው ብለዋል። እንደ ሀገር ኢንተርፕራይዞች የኢኮኖሚያችን የጀርባ አጥንት ናቸው፤ ዘርፉ የሥራ ዕድል በመፍጠር እና ኢኮኖሚውን በማነቃቃትም የጎላ አቅም እንዳላቸው ተናግረዋል።

መርሐ ግብሩ በሁሉም ክልሎች እንደሚቀጥልም ተመላክቷል።

ዘጋቢ:- ሰለሞን አሰፌ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የትምህርት ዘርፉ የሁሉም የልማት ሥራዎቻችን መሪ ተግባር ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next article“ኢትዮጵያ በዘመናዊና አረንጓዴ ትራንስፖርት ዓለምን ለመምራት ዝግጁ ናት” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ