
በከተማዋ ጅብሩክ እየተባለ በሚጠራው ጥንታዊ ስፍራ የተከሰተው የእሳት አደጋ በአካባቢው የነበሩ ሱቆችን ሙሉ በሙሉ አውድሟል፡፡ ነጋዴዎቹ ልብስ በመስፋት ስራ ላይ የተሰማሩ ነበሩ፤ በአንድ ሱቅ ውስጥም ከአንድ እስከ አራት የልብስ ስፌት ማሽኖች ይገኙ እንደነበር ተጎጂ ነጋዴዎቹ ገልፀዋል፡፡
የከተማዋ ወጣቶች ተጎጅዎችን ለመደገፍ የሚያስችል ገንዘብ ማሰባሰብ ሥራን በህጋዊ መንገድ እንደጀመሩም ታውቋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ የሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን ዋና ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ከበደ በሽር እንደገለፁት በስፍራው ጥበቃ እየተደረገ መሆኑን አና የእሳት አደጋውን መንስኤ በመጣራት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለመደገፍም ሁሉም መረባረብ እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፦ሕይወት አስማማው