በአማራ ክልል በ 24 ሰዓታት የኮሮናቫይረስ ምርመራ የተደረገላቸው ሁሉም ከቫይረሱ ነጻ ሆነዋል፡፡

194

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 18/2012 ዓ.ም (አብመድ) በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ለ694 ናሙናዎች ምርመራ ተደርጎ ዛሬም ሁሉም ሰዎች ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አረጋግጧል፡፡

በ24 ሰዓታት ከቫይረሱ ያገገመ፣ ወደ ጽኑ ህሙማን ህክምና ክፍል የገባም ሆነ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወቱ ያለፈ አለመኖሩንም ቢሮው አስታውቋል።

በአማራ ክልል እስከ ዛሬ ሰኔ 18/2012 ዓ.ም ድረስ ለ12 ሺህ 574 ሰዎች የናሙና ምርመራ ተደርጎ በ277 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡

ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ሕክምና መስጫ ማዕከላት የሚገኙ ሁሉም ታካሚዎች በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙም ቢሮው አስታውቋል፡፡

እስከዛሬ በክልሉ 84 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፤ ሁለት ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመላክተታል።

በደጀኔ በቀለ

Previous articleማዕድን አውጪውን በአንድ ጊዜ ሚሊዬነር ያደረገው አጋጣሚ!
Next articleበደሴ ከተማ የተነሳ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ከ86 በላይ የቤተሰብ አስተዳዳሪዎችን ለጉዳት ዳረገ፡፡