በጎንደር ከተማ አሥተዳደር ከ800 ሄክታር በላይ መሬት የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ ይሠራል።

3
ጎንደር: ታኅሣሥ 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ አሥተዳደር የ2018 ዓ.ም የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በድባ ደፈጫ ቀበሌ ተካሂዷል።
በጎንደር ከተማ አሥተዳደር የድባ ደፈጫ ቀበሌ አርሶ አደሮች በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ በየዓመቱ ሲሳተፉ መቆየታቸውን ገልጸዋል።
የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ ያለውን ጠቀሜታ የተረዱት አርሶ አደሮቹ በተፋሰስ ሥራዎች ላይ ሲሳተፉ መቆየታቸውን ገልጸው በቀጣይም የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራው ከመጀመሩ በፊት የተፋሰስ ልየታ፣ የሚሠራ የሰው ኀይል ልየታ እና ቀያሽ አርሶ አደሮችን የማዘጋጀት ሥራ ሲከናወን መቆየቱን የጎንደር ከተማ
አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ኀላፊ አበራ አደባ ገልጸዋል።
በከተማ አሥተዳደሩ በሚገኙ 11 የገጠር ቀበሌዎች የአፈር እና ውኃ ጥበቃ ሥራ በ18 ተፋሰሶች እና
በ897 ሄክታር መሬት እንደሚሠራ መምሪያ ኀላፊው ጠቅሰዋል።
በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራው ከ8ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተሳታፊ እንደሚኾኑም ተናግረዋል።
አሁን የሚሠሩ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራዎችን በሥነ ሕይወታዊ መንገድ የማጠናከር ሥራ በቀጣይም ይከናወናል ተብሏል።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራው በ11 የገጠር ቀበሌዎች ይሠራል ብለዋል።
ይህ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ ከተማው የንጹህ መጠጥ ውኃ በበቂ እንዲያገኝ ያለው ድርሻ ትልቅ እንደኾነ ጠቅሰዋል።
አርሶ አደሮች የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ ያለውን ጠቀሜታ በመረዳት ባለቤት ኾነው በየዓመቱ እየሠሩ መኾናቸውንም ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው አብራርተዋል።
የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራው ለ30 ቀናት የሚቀጥል መኾኑን የጠቀሱት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ይህም ተግባር ውጤታማ እንዲኾን በጀት ከመመደብ ጀምሮ ለሥራው ግብዓትን
በማቅረብ እየተሠራ እንደኾነ ገልጸዋል።
የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራው በየዓመቱ የአካባቢውን ማኅበረሰብ በማሳተፍ ዘላቂ ጠቀሜታ እንዲሰጥ እየተሠራበት ይገኛል ተብሏል።
ዘጋቢ:- ዳንኤል ወርቄ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበግብርናው ዘርፍ ቴክኖሎጂን የመጠቀም ልምዱ እያደገ መጥቷል።
Next articleየዲጂታል አማራ ስትራቴጅ የአሠልጣኞች ሥልጠና መርሐ ግብር በጎንደር ከተማ ተጀምሯል።