በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ዘንዘልማ ቀበሌ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራ በይፋ ተጀምሯል።

5
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራው በ12 ቀበሌዎች በ24 ተፋሠሶች ይሠራል። ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው በማሥጀመሪያ መርኃ ግብሩ ላይ እንዳሉት የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራ የሚከናወንባቸው ቀበሌዎች የዓባይ እና ጣና ተፋሰስ መሆናቸው ሐይቁ እና ወንዙ በደለል እንዳይሞሉ ወሳኝነት አለው ብለዋል።
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኀላፊ መሰሉ ብርሃኑ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የተፋሰስ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል። እስከአሁንም ከ1 ሺህ 600 በላይ በሆኑ ተፋሰሶች ከ3 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የተፋሠስ ሥራ ተሠርቷል ብለዋል። በዚህ ዓመትም ልማትን ሊያረጋግጥ በሚችል አግባብ ቀድመው የተሠሩትን ማጠናከር፤ በአዲስ የሚሠሩትን በጥራት መሥራት ትኩረት ይደረግበታል ብለዋል።
የዘንዘልማ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደሮች ባለፋት ዓመታት በተሠራው ሥራ መሬታቸው ለምነቱ ተመልሶ ምርታማነታቸው እንዲጨምር እንደረዳቸው አሥረድተዋል። የዚህን ዓመት የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራም ዘላቂ ልማትን ሊያረጋግጥ በሚችል መንገድ እንደሚሠሩ ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበጎንደር ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብሩ የወተት ምርት በ10 ቀበሌዎች እየተተገበረ ነው።
Next articleበኤርትራ መንግሥት በቀይ ባሕር አፋር ሕዝቦች ላይ እየደረሰ ያለውን ስልታዊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለማስቆም አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ተቋማት ጫና እንዲያሳድሩ የቀይ ባሕር አፋሮች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ጥሪ አቀረበ።