ሰላምን ለማረጋገጥ ቅድሚያ አንድነትን ማጠናከር ያስፈልጋል።

3
ገንዳ ውኃ: ታኅሣሥ 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር የሰላም ኮንፈረንስ በጉባይ ቀበሌ ተካሂዷል።
መንግሥት እያደረገ ያለውን ሕግ የማስከበር ተግባር ሊያጠናክር እንደሚገባ ተሳታፊዎች አሳስበዋል።
ለሰላም መከበር የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተሳታፊዎች ገልጸው የልማት ተጠቃሚ እንዲኾኑም ጠይቀዋል።
ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የሀገር ሽማግሌዎች ሚና ከፍተኛ መኾኑን ተሳታፊዎች ጠቅሰው እያደረጉት ያለው ጥረት አጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል።
ወጣቶች ለሰላም መስፈን የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ እንመክራለን ብለዋል።
የመተማ ወረዳ ምክትል ዋና አሥተዳዳሪ ግዛት ሰርፀ ማኅበረሰቡ ለአካባቢው ሰላም ቁርጠኛ በመኾን ሁለንተናዊ ሰላምን ማስፈን ይጠበቅበታል ብለዋል።
የጸጥታ መዋቅሩን በማጠናከር ሰላምን ለማጽናት ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ደረሰ አዱኛ ሕዝቡ በሰላም እጦቱ የችግር ገፈት ቀማሽ ኾኖ መቆየቱን አስታውሰው አሁን ኅብረተሰቡ በሰላም እና ልማት ዙሪያ ተጠቃሚ እንዲኾን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው ብለዋል።
ለሕዝብ እና ለሀገር ሰላም ሲባል የታጠቁ አካላት የሰላሙን ጥሪ ተቀብለው ወደ ማኅበረሰቡ መቀላቀል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
በሀገር መከላከያ ሠራዊት የጦር አዛዥ ኮሎኔል ሰለሞን አፈራ በበኩላቸው ሰላምን ለማፅናት ከመከፋፈል ወጥተን በአንድነት የአካባቢውን ሰላም በጋራ መጠበቅ እንደሚገባ አስረድተዋል።
መከላከያ ለሕዝብ ሰላም የቆመ እና ሕግን የሚያስከበር መኾኑን በመረዳት ሕዝቡ ከሠራዊቱ ጎን በመቆም ድጋፍ ማድረግ አለበት ብለዋል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኀላፊ አንዳርጌ ጌጡ ሰላም የሁሉም ነገር መሠረት መኾኑን በመረዳት ማኅበረሰቡ ለሰላም መጽናት ርብርብ ማድረግ እንዳለበት ተናግረዋል።
አሁን ያለውን አንፃራዊ ሰላም ወደ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ማኅበረሰቡ አንድነቱን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ነው ያሉት።
በዕለቱ ታጥቀው ሲቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ማኅበረሰቡ ተቀላቅለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየአማራ ክልል ምክር ቤት የ6ኛው ዙር፣ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 11ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከታኅሣሥ 16-17/2018 ዓ .ም ይካሄዳል።
Next articleበጎንደር ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብሩ የወተት ምርት በ10 ቀበሌዎች እየተተገበረ ነው።