
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጉባኤው ከታኅሣሥ 16-17/2018 ዓ .ም እንደሚካሄድ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
በእነዚህ ቀናቶች የትምህርት አጀማመር እና እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት፣ ያጋጠሙ ችግሮች፣ የኦዲት ግኝቶች እና ሌሎች ልዩ ልዩ አጀንዳዎች በእለቱ እንደሚቀርቡ እና ውይይት እንደሚደረግባቸው ገልጸዋል።የምክር ቤት አባላት ወደ ምክር ቤት የሚመጡበት አንዱ እና ዋነኛው አላማ በየአካባቢያቸው የተሠሩ መልካም ሥራዎች ምንድን ናቸው የሚለውን እና መፍትሄ የሚፈልጉትን ደግሞ ለሚመለከተው አካል ለማቅረብ ነው ብለዋል።
በዘንድሮው በጀት ዓመት እቅድን መሰረት ያደረገ በጀት ፀድቋል ነው ያሉት።አባላቱ እቅዱን መሰረት በማድረግ እንደየ አካባቢያቸው አፈፃፀሙ ምን ይመስላል የሚለውን ከየምርጫ ክልላቸው ሀሳብ ይዘው የሚመጡበት ነውም ብለዋል።
ክልሉ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ የሚያውቁበት ጉባኤም ነው ያሉት።ጉባኤው ለቀጣይ ሥራም ስንቅ የሚኾኑ መረጃዎች የሚሰጡበት እንደኾነም ዋና አፈ ጉባኤዋ ተናግረዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
