በደብረ ማርቆስ የሰላም ጥሪን ተቀብለው ከመጡ ታጣቂዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።

3

ደብረ ማርቆስ: ታኅሣሥ 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ወደ ሰላም የመጡ ታጣቂዎች በተደረገው ውይይት የቆዩበት የትጥቅ ትግል ሕዝቡን ለውስብስብ ስቃይ እና እንግልት ዳርጎ መቆየቱን ተናግረዋል።

በቆዩበት የጥፋት መንገድ እንደተጸጸቱ የገለጹት ታጣቂዎቹ በሰላማዊ የትግል መንገድ የበደሉትን ማኅበረሰብ ለመካስ እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል።

ትግሉ መቋጫ እንዳያገኝ የሚሠሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታረሙ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት ታጣቂዎቹ ወደ ሰላም ለሚመጡ ወጣቶች የሥራ እድል እንዲመቻችላቸው ጠይቀዋል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኀላፊ ይኸነው አበባው ታጣቂ ኀይሎች የቆዩበት ትግል የሕዝቡን ስቃይ ከማራዘም ውጭ ያስገኘው ውጤት አለመኖሩን በመገንዘብ ከእልህና ከስሜት መውጣት ያስፈልጋል ብለዋል።

የሰላም ጥሪ የተቀበሉ አካላትን ሥልጠና በመስጠት በሥራ እድል ለማቋቋም እየተሠራ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ግጭቱ ማጣት የማይገባንን ሰብአዊ ሕይወት በማሳጣት በተፈፀሙ ድርጊቶች ወጣቶችን ለሥነ ልቦና ጫና እየዳረጉ መኾኑን የገለጹት በብልጽግና ፓርቲ የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ መልካሙ ሽባባው ናቸው።

ከታጠቁ ኀይሎች ጋር ትስስር ፈጥረው ግጭቱን የሚያባብሱ አካላት ላይ የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ለሰላም ዋጋ መክፈል አለብን ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየታጣቂ ኀይሎች ለሰላም ቅድሚያ እንዲሰጡ ምሁራን ኅላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ። ‎
Next article“በባሕላዊ መንገድ ከቀፎ 10 ኪ.ግ የማይበልጥ የነበረው የማር ምርት አሁን 50 ኪ.ግ ድረስ ማምረት ችለናል” አናቢዎች