የሙስና ወንጀልን መከላከል የሁሉም ድርሻ ሊኾን ይገባል።

3

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ እና የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በሙስና ወንጀል ምርመራ እና ክስ አመሠራረት የቅንጅት ሥራ ላይ ውይይት እያደረጉ ነው።

በውይይቱ የተገኙት የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኀላፊ ብርሃኑ ጎሽም እንዳሉት የሕዝብን ደኅንነት ለማረጋገጥ፣ የመንግሥት እና የሕዝብ ሀብት ለታለመለት አላማ እንዲውል መከታተል የፍትሕ ተቋማት ኀላፊነት ነው።

ከወንጀል መከላከል ጀምሮ በምርመራ፣ በክስ፣ በክርክር፣ ጥፋተኞችም ታርመው ጥሩ ዜጋ ኾነው እንዲወጡ የፍትሕ እና የፖሊስ ተቋማት ቅንጅታዊ አሠራር እንደሚጠይቅ አንስተዋል።

በተለይም ደግሞ አሁን ላይ በክልሉ አስጊ እየኾነ የመጣውን የሙስና ወንጀል ለመከላከል እና አጥፊዎችን ተጠያቂ ለማድረግ የፍትሕ ተቋማቱ ተቀናጅተው እየሠሩ መኾኑን ገልጸዋል።

ትውልድን በሥነ ምግባር፣ ተቋምን ደግሞ በአሠራር በማጠናከር በክልሉ ያለውን የሙስና ወንጀል መከላከል የሁሉም ድርሻ ሊኾን ይገባል ብለዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ (ዶ.ር) ሙስና የጥቂቶች መበልጸጊያ ነው ብለዋልል።

በክልሉ የሚታየውን ብልሹ አሠራር እና ሙስና በመከላከል የክልሉን ሰላም ማረጋገጥ አንዱ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ መኾኑን ገልጸዋል።

ለዚህ ደግሞ ፍትሕ ቢሮ እና ፖሊስ ተቀናጅተው እየሠሩ ነው። የፖሊስን የምርመራ አቅም የማጎልበት ሥራም እየተሠራ መኾኑንም ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በዱር ቤቴ ከተማ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ።
Next articleለበዓል ወደ ላሊበላ የሚገቡ እንግዶችን ለማስተናገድ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል።