መንግሥት የሠራተኞችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ያደረገውን ጥናት ማጠናቀቁን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።

702

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 18/2012 ዓ.ም (አብመድ) አነስተኛ ደሞዝ የሚከፈላቸው የመንግሥት ሠራተኞችን የመኖሪያ ቤት ጫና የሚያቃልል ጥናት አስጠንቶ ለመንግሥት ሊያቀርብ መሆኑን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የመንግሥት ሠራተኞች ለረጅም ዓመታት በምሬት ከሚያነሷቸው ችግሮች አንዱና ዋነኛው የመኖሪያ ቤት ችግር ነው። በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኑሮ ውድነቱ ከቤት ኪራይ ዋጋ መናር ጋር ተዳምሮ የዜጎችን ኑሮ እየፈተነ ይገኛል።

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር በዛብህ ገብረየስ ለኢዜአ እንደገለጹት በቤት ኪራይ ዋጋ መናር ቀጥተኛ ተጎጂ ከሚሆኑ ዜጎች መካከል ዝቅተኛ ደመወዝ የሚከፈላቸው የመንግሥት ሠራተኞች ይጠቀሳሉ።

ሠራተኞቹ ገቢያቸውን በሙሉ ለቤት ኪራይ ስለሚያውሉ ምግብና ሌሎች አገልግሎቶችን ለመሸፈን እንደሚቸገሩ አስረድተዋል።

ችግሩን ይፈታል የተባለ ጥናት ኮሚሽኑ ከከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ጋር በመሆን ጥናት ማስጠናቱንና ጥናቱም በቅርቡ ለመንግሥት እንደሚቀርብ ገልጸዋል።

”በዋነኛነት ለረጅም ዓመታት በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሲሰሩ ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ደመዝ የሚኖሩ ሰዎች አሁን ላይ ከተፈጠረው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ መናርና ሌሎችም ተያያዥ ችግሮች ጋር ተያይዞ የሚበሉበትን እስከማጣት የሚደርሱ መሆናቸውን ጥናቶቻችን አሳይተውናል” ብለዋል ኮሚሽነሩ።

Previous articleየኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ህወሐትን ከጥምረቱ አባልነት መሰረዙን አስታወቀ።
Next articleማዕድን አውጪውን በአንድ ጊዜ ሚሊዬነር ያደረገው አጋጣሚ!