የባሕር በር ጥያቄ እንዲሳካ ከመንግሥት ጎን እንደሚቆሙ የሐይቅ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

5

ደሴ: ታኅሣሥ 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር በር ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ እድገት እና አጠቃላይ ደኅንነት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው መኾኑን የሐይቅ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ሻምበል መኮንን አሊ በውትድርና ሙያ ሀገራቸውን ሲያገለግሉ ሳለ ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት የነበረችበትን ወቅት ያስታውሳሉ። አሁን ላይ በቁጭት እና በሀዘን ስሜት ውስጥ እንደኾኑም ገልጸዋል።

አሰብ ወደብን አውቀዋለሁ መሠረተ ልማቱን ሁሉ በጊዜው የገነባው የኢትዮጵያ መንግሥት ነው ያሉት ሻምበል መኮንን የኢትዮጵያ ሃብት የፈሰሰበት እና ኢትዮጵያውያን የተሰውበት ነው ብለዋል። የአሰብ ወደብን ኢትዮጵያ ያጣችበት መንገድ ሁሌም ሲከነክናቸው እንደሚኖርም ነው የገለጹት።

በአሁኑ ወቅት መንግሥት እንደ ሀገር የባሕር በር ያስፈልገናል በሚል የያዘው እቅድ እንዳስደሰታቸው እና ኢትዮጵያም የባሕር በር እንደሚኖራት ተስፋ መሰነቃቸውን ነው የተናገሩት።

ሌላኛዋ የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ እናትነሽ በሽር የባሕር በር በማጣታችን እንደ ሀገር የኢኮኖሚ እድገታችን ተገቷል፤ የባሕር በር ቢኖረን እስካሁን የተሻለ ኢኮኖሚ እንገነባ ነበር ብለዋል።

የቀድሞ መምህር የኾኑት ስለሺ አለልኝ እና ወጣት አሰፋ ሰጠ በሕወሃት ዘመነ መንግሥት የባሕር በር ጉዳይ ኾን ተብሎ እንዳይነሳ እና ጉዳዩም እንዲረሳ መሠራቱን ነው የገለጹት።

የባሕር በር በዓለም አቀፍ ደረጃ የሀገራችንን ተቀባይነት የሚያሳድግ በመኾኑ ለተግባራዊነቱ በጋራ መቆም እንደሚያስፈልግ ነዋሪዎቹ አስረድተዋል።

መንግሥት የያዘውን የባሕር በር አጀንዳ እንደሚደግፉ እና ለውጤታማነቱም ከመንግሥት ጎን እንደሚቆሙ ተናግረዋል።

ዘጋቢ:- ከድር አሊ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበኩር ጋዜጣ ታኅሣሥ 13/2018 ዓ.ም
Next articleነጻ የሕግ ድጋፍ ምንድን ነው?