
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 18/2012 ዓ.ም (አብመድ) ጥምረቱ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው በ4ኛው መደበኛ ጠቅላላ መደበኛ ጉባዔው ነው፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ህወሐትን ከጥምረቱ የሰረዘበት ምክንያት የጥምረቱን መተዳደሪያ ደንብን ባለመክበሩ መሆኑን ገልጿል።
ጥምረቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን አስመልክቶ ምርጫ እንደማይኖር ወይም ደግሞ የምርጫው መካሄድ ተገቢ እንዳልሆና መክሯል፡፡
በሀገሪቱ ላይ ሰላምና ጸጥታ ሊሰፍን በሚችልባቸው ሀሳቦችም ላይ ውይይት ማድረጉም ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ሊቀመንበር አቶ ደረጀ በቀለ እንደተናገሩት ህወሐት ከአንድም ሁለት ጊዜ በተጠራው ስብሰባ ላይም አልተገኘም፡፡
አዲስ አበባ ላይ የሚካሄዱ ስብሰባዎችን ህወሐት ለሀገር መግባባት በማይጠቅምና አፍራሽ በሆነ አካሄድ ህገ ወጥ ናቸው የሚል ግፊት ሲያደርግባቸው እንደነበርም ሊቀመንበሩ ተናግረዋል፡፡
ኢብኮ እንደዘገበው በተቃራኒው ደግሞ ስብሰባዎቹ በመቀለ ከተማ ይደረጉ የሚል ግፊት ሲደረግብን ነበር ብለዋል አቶ ደረጀ፡፡