በደሴ እና አካበቢዋ ባለው የአየር ፀባይ ምክንያት ዛሬ እና ነገ በረራዎች አይኖሩም።

1
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ሰዓት በደሴ እና አካበቢዋ ባለው ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ፀባይ ምክንያት በዛሬው እና በነገው ዕለት ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን በረራ ለማቋረጥ መገደዱን አሳውቋል።
ከሚቲዎሮሎጂ በሚገኘው መረጃ መሰረት የአየር ፀባዩ እንደተስተካከለ በረራዎቹ ወደ መደበኛ አገልግሎታቸው የሚመለሱበትን ጊዜ እንደሚያሳውቅ አየር መንገዱ ገልጿል። በአገልግሎቱ መቋረጥ ለሚፈጠሩ መጉላላቶችም ከወዲሁ ይቅርታ ለመጠየቅ እንወዳለን ብሏል አየር መንገዱ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleከ24 ሺህ በላይ ወጣቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ እየሠራ መኾኑን የምዕራብ ጎንደር ዞን ሥራ እና ክህሎት መምሪያ አስታወቀ።
Next articleፍርድ ቤቱ የሕዝብ እንግልትን ለመቀነስ የለውጥ ተግባራትን እያከናወነ ነው።