
ናሳ ቀልድ አዋቂ ግለሰቦችን በጠፈርተኛነት ሊቀጥር ነው፡፡
የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ድርጅት ቀልድ አዋቂ ግለሰቦችን በጠፈርተኛነት ሊቀጥር ነው፡፡
የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ድርጅት (ናሳ) ቀልደኛ እና አዝናኝ ሰዎችን በጠፈርተኝነት ለመቅጠር እየተዘጋጀ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ጠፈርተኞች በተለምዶ ቁም ነገረኞች እና ቁጥቦች እንዲሁም በቢሊዮን ዶላር የሚገመቱ መሣሪያዎችን የሚያበሩ ኃላፊነት ተሸካሚዎች ናቸው ተብሎ ይታሰባል፡፡
ቀልድ አዋቂ እና አዝናኝ ግለሰቦችን መቅጠር ረዥም እና አሰልች የጠፈር ጉዞዎችን አዝናኝ እና አስደሳች ለማድረግ እንደሚረዳ በጥናት አረጋግጫለሁ ብሎ ነው ናሳ ቀልድ አዋቂዎችንና አዝናኞችን መቅጠር የፈለገው፡፡
ምጥን ቀልድ እና ጨዋታ የማንኛውንም የሥራ ቡድን ውጤታማ ያደርጋል ያለው ድርጅቱ በቀጣዩ 2030 (እ.አ.አ) ለሚደረገው የማርስ ተልዕኮ ከሚጓዙጠፈርተኞች ጋር ቀልድ አዋቂዎች አብረው እንደሚጓዙ አሳውቋል፡፡ ‹‹አሰልችውን የሁለት ዓመት የጠፈር ላይ ጉዞ አዝናኝ እና አስደሳች ያደርጋሉ፤ በዚህምየጠፈርተኞች ቡድኑን መንፈስ ሁሌም የተነሳሳ እንዲሆን ያደርጋሉ›› ነው የተባለው፡፡ በተከታታይ የሙከራ በረራዎች ላይ ቀልድ አዋቂዎችን የመመልመል ሥራውእንደሚከናወንም ናሳ ይፋ አድርጓል፡፡
ምንጭ፡ ዴይሊ ሜል
በቢኒያም መስፍን