በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪውን ተቀበሉ።

5

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።

ታጥቀው በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ሰሞኑን በተከታታይ ወደ ሰላም እየገቡ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ራሱን “አፋብኃ መብረቅ ክፍለ ጦር ቁልቋል በር ብርጌድ” ብሎ የሚጠራው ቡድን መሪ አዘዘ ሞላን ጨምሮ 17 የቡድኑ አባላት 1 ብሬን፣ 5 ክላሽ፣ 1 የጦር ሜዳ መነፅር፣ 3 ምኒሽር፣ 2 ችኮዝ፣ 1 ማስ፣ 1 ጓንዴ እና 1 አልቢን በመያዝ የሰላም ጥሪውን በመቀበል ገብተዋል።

ወደ ሰላም የገቡት የታጣቂው ቡድን አባላት እንደተናገሩት መንግስት የሕዝቡን ጥያቄ እንደሚፈታ በማመናቸው የሰላም አማራጭን መቀበላቸውን ገልፀው ከመንግስት እና ከሕዝብ ጎን በመሰለፍ ሌሎች በጫካ የሚኖሩ ወንድሞችም ወደ ሰላም የሚመጡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ዝግጁ መኾናቸውን ገልፀዋል።

መንግስት በተከታታይ ሲያደርግላቸው የነበረውን የሰላምና ጥሪ መቀበላቸው ትክክለኛ ምርጫ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።

መረጃው የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ የግብር ከፋዮችን ገቢ ያማከለ ሥርዓት እንዲኖር ትልቅ ሚና ያለው ነው።
Next articleሁሉም ለሰላም እንዲቆም ጥሪ ቀረበ።