“እያንዳንዱ ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ ታክስ ላይ ተጽዕኖ አለው” መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር)

5

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ለተለያዩ የሕግ ባለሙያዎች፣ ለአጋር እና ለባለድርሻ አካላት በተሻሻለው የፌዴራል የግብር አዋጅ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጁ ላይ ሥልጠና እየሰጠ ነው።

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) የግብር አሰባሰባችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ነው ብለዋል። በዚያው ልክ ደግሞ የወጭ ፍላጎታችንም እየጨመረ እንደኾነ ነው የገለጹት።

የሕዝባችን የመልማት ጥያቄ እና የሠራተኞች የደመወዝ ጥያቄ በጣም እየሠፋ እና እያደገ ነው ብለዋል። ይህን ተደራሽ ለማድረግ ደግሞ አዋጆችን በአግባቡ ማጽደቅ እና ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ነው ያሉት።

ሕገ ወጥነትን በተለይም ደግሞ ከኮንትሮባንድ ጋር በተያያዘ እና ሕገ ወጥ ንግድ ለአዋጁ መተግበር ተጽዕኖ እንዳለው አንስተዋል። ታክስን የማይነካ ነገር የለም፤ “እያንዳንዱ ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ ታክስ ላይ ተጽዕኖ አለው” ብለዋል ።

አሁን የወጣው የገቢ የግብር ረቂቅ አዋጅ የግብር ማጭበርበርን እና የግብር ስወራን መከላከል የሚያስችል እንደኾነ ነው የገለጹት።

ትክክለኛ ግብር ከፋይ፣ ትክክለኛ ነጋዴ እና የንግድ ሕጉን አክብሮ የሚንቀሳቀስ ግብር ከፋይ ሲኖር ነው ታክስም ኾነ ግብር መጨመር የሚችለው ብለዋል።

ማንኛውም ግብር ከፋይ ገቢውን ያገናዘበ እና ፍትሐዊ ግብር መክፈል እንዳለበትም አሳስበዋል።

ዘጋቢ:- ሰመሀል ፍስሀ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሃይማኖት አባቶች ደኖች እንዲጠበቁ በማድረግ በኩል ትልቅ ባለውለታዎች ናቸው።
Next article“ልዩነቶች መፈታት ያለባቸው በሀሳብ የበላይነት ብቻ ሊኾን ይገባል” ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)