“ከትምህርት የራቀ ትውልድ ከድህነት አዙሪት ሊወጣ አይችልም” አቶ ካሳሁን አዳነ

17
ደብረ ብርሃን: ታኅሣሥ 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ቢሮ እና በሰሜን ሸዋ ዞን የትምህርት መምሪያ የሥራ ኀላፊዎች በዞኑ በተገኙበት በተጀመሩ መልካም ሥራዎች፣ መፈታት ያለባቸው ችግሮች እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ምክክር ተካሂዷል።
በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት እና ትግበራ ዳይሬክቶሬት የፊዚክስ ባለሙያው አለኸኝ መልካሙ በተለያዩ ወረዳዎች እና ትምህርት ቤቶች በተደረገ ጉብኝት መልካም ጅምሮች መኖራቸውን ተናግረዋል።
አሁንም ቢኾን በየደረጃው የሚገኝ የትምህርት መዋቅር ሥራውን በባለቤትነት የመያዝ ማኅበረሰቡን አጋር በማድረግ በውጤት የሚለካ ትግበራ ይጠይቃል ነው ያሉት ባለሙያው።
በዞኑ 62 በመቶ ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ መሆናቸውን የጠቀሱት ደግሞ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ጸጋዬ እንግዳወርቅ ናቸው። አመለካከት፣ ዕውቀት እና ክህሎት መገንባት ዋና ትኩረታችን ነው ብለዋል።
ለዚህም የመምሪያው ባለሙያዎች በየትምህርት ተቋማት ችግሮችን መለየት እና የጎደለውን ለመሙላት የሚያስችል ስምሪት ይሰጣል ሲሉም ገልጸዋል።
እንደ ክልል ትምህርት ላይ የገጠመንን ችግር ለመፍታት እየተሠራ ባለው ተግባር ይህ ዓመት የተሻለ እንቅስቃሴ የታየበት ነው ያሉት ደግሞ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አማካሪ ካሳሁን አዳነ ናቸው። አሁንም የባለድርሻ አካላትን ሚና ይጠይቃል ነው ያሉት።
ከዕውቀት የተፋታ ትውልድ ከድህነት እና ኋላቀርነት ሊወጣ አይችልም ያሉት ምክትል ቢሮ ኀላፊው የኢትዮጵያን ቀጣይ ዕጣ ፈንታ በሚወስኑ የትምህርት ተቋማት እና ትውልድ ግንባታ ላይ መሥራት ይገባል ሲሉም ገልጸዋል።
በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች ቁጥር ዝቅተኛ መኾኑንም ተናግረዋል። ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት መላክ እና ተቋማትን መደገፍ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ይጠበቃልም ነው ያሉት።
ዘጋቢ:- በላይ ተስፋዬ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ምሁራን ካስተማራቸው ሕዝብ ጎን ቁመው ለሰላም እና ልማት መሥራት ያለባቸው ሰዓት አሁን ነው” አቶ ይርጋ ሲሳይ
Next articleስለስትሮክ ምን ያህል በቂ ግንዛቤ አለዎት?