ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የጀመረበትን 10ኛ ዓመት እያከበረ ነው።

4
አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ባንኩ “ንብ ሃላል” የሚል ስያሜ ያለው የኅብረተሰቡን የፋይናንስ ፍላጎት ለማሟላት የሸሪዓ ሕጎችን ባከበረ መልኩ ተደራሽ ለመኾን ሢሠራ ቆይቷል ።
ባንኩ በሚሰጠው አገልግሎት በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እያደረገ መኾኑን የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ ስብሰቢ መሐመድ ዘይን (ዶ.ር) ተናግረዋል።
ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት የሸሪዓ ሕግን መሠረት በማድረግ የሸሪዓ ሕግ አማካሪ ኮሚቴ በማቋቋም ይሠራል ብለዋል።
የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሺህሰማ ሸዋነካ ባንኩ የገጠመውን ችግር እና ፈተና በመቋቋም አሁን ላይ ስኬት ላይ ሆኖ ከወለድ ነጻ አገልግሎት የጀመረበትን 10ኛ ዓመት እያከበረ በመኾኑ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
ከወለድ ነጻ አገልግሎቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ደምበኞችን ለማፍራት ማስቻሉን እና የፋይናንስ ተቋማት አካታችነትን የሚያረጋግጥ መኾኑን የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ሄኖክ ከበደ ተናግረዋል።
በአሁኑ ጊዜ ባንኩ ከወለድ ነጻ አገልግሎት ብቻ የሚሰጡ ቅርንጫፎችን ከዘጠኝ ወደ 23 ማድረስ ችሏል። በቀጣይም አገልግሎቱን በማስፋት ዘመናዊነትን በመላበስ እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡ ፡
ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት በዓለም መሰጠት ከተጀመረ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ተቆጥሯል ነው ያሉት። በዓለም ከስድስት ትሪሊዮን ዶላር በላይ የሚንቀሳቀስበት ዘርፍም ኾኗል። በኢትዮጵያም በ20ዐ6 ዓ.ም አገልግሎቱ መሠጠት የተጀመረ ሲኾን 24 ባንኮች አገልግሎቱን ይሠጣሉ።
የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ንብ ሃላል 10ኛ ዓመት በደም ልገሳ እና በተለያዩ መርሐ ግብሮች ለቀጣይ ሦስት ወራት እንደሚከበር ተገልጿል።
ንብ ሃላል ለ10 ዓመታት ይጠቀምበት የነበረውን መለያ በአዲስ ቀይሯል። የንብ ኢንተርናሽናል ባንክን ቀለሞች በመጠቀም ንብ ሃላል የቀለም ለውጥ እና ለዕይታ እንዲመች ኾኖ መሻሻሉም ተገልጿል።
ዘጋቢ:- ሠላማዊት ነጋ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ሐጂ ማድረግ የሚያከስር ሳይኾን ሃብትንም የሚያበረክት ነው” ሼህ ኑረዲን ቃሲም
Next articleየጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መልእክት፦