ትምህርት ቤቶችን በጥራት በመገንባት ደረጃቸውን ማሻሻል ያስፈልጋል።

4
ደብረ ማርቆስ: ታኅሣሥ 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ደምስ እንድሪስ በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር በፌደራል መንግሥት ድጋፍ፣ በአልማ እና በማኅበረሰብ አስዋጽኦ እየተገነቡ ያሉ የትምህርት ተቋማት የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል።
የከተማ አሥተዳደሩ አማራ ልማት ማኅበር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አየነው መኮንን በአልማ እና በማኅበረሰብ ተሳትፎ የሚገነቡ ትምህርት ቤቶችን ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለማጠናቀቅ እየሠሩ ስለመኾኑ ገልጸዋል።
የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ስለሺ ተመሥገን የትምህርት ተቋማት ግንባታዎች በጥራት እና በተያዘላቸው ጊዜ ተጠናቅቀው ለኅብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ክትትል ይደረጋል ብለዋል።
የመስክ ምልከታ ያደረጉት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ደምስ እንድሪስ በፌደራል የገንዘብ ድጋፍ እየተገነባ የሚገኘው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተያዘለት ጊዜ በጥራት ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ ክትትል እና ድጋፍ ያስፈልጋል ብለዋል።
በተመሳሳይ በከተማ አሥተዳደሩ በአልማ እና በማኅበረሰቡ እየተገነቡ ያሉ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በጥራት በመገንባት የትምሕርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል ይጠበቃል ነው ያሉት።
በከተማ አሥተዳደሩ እየተገነባ ያለው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፌደራል መንግሥት ወጭ የሚገነባ ሲኾን ከ485 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦለት ወደ ሥራ መገባቱ ተገልጿል።
ምክትል ቢሮ ኀላፊው በከተማ አሥተዳደሩ ከሚገነቡ የትምህርት ተቋማት በተጨማሪ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎችን የምገባ እና የመማር ማስተማር ሂደትንም ተመልክተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous article“የኢትዮጵያ እና ሕንድ የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleችግሮችን የሚሸከም ትከሻ ያለው የፓርቲ አባል በመገንባት ኢትዮጵያን ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል።