
በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ለ462 ናሙናዎች ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ሰዎች ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አረጋግጧል፡፡
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ እንዳስታወቀው ባለፉት 24 ሰዓታት ከቫይረሱ ያገገመ፣ ወደ ጽኑ ህሙማን ህክምና ክፍል የገባም ሆነ በቫይረሱ ምክንያት ህይወቱ ያለፈ የለም፡፡
በአማራ ክልል እስከ ዛሬ ሰኔ 17/2012 ዓ.ም ድረስ ለ11 ሺህ 880 ሰዎች የናሙና ምርመራ ተደርጎ በ277 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡
ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ሕክምና መስጫ ማዕከላት የሚገኙ ሁሉም ታካሚዎች በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙም ቢሮው አስታውቋል፡፡
እስከዛሬ በክልሉ 84 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፤ ሁለት ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡
በደጀኔ በቀለ
