
ደብረ ብርሃን፡ ታኅሣሥ 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ቃል በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ የተካሄደው ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ተጠናቋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት በደብረ ብርሃን ከተማ በርካታ የልማት ሥራዎች መሠራታቸውን በመድረኩ አንስተዋል።
በቀጣይ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን በማስቀጠል እና የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን በመፍታት ደብረ ብርሃን ከተማን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ሥራዎች ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ደብረ ብርሃን እንደ ስሟ የብልጽግና ብርሃን እየፈነጠቀባት ያለች ከተማ ነች ያሉት ደግሞ የደቡብ ምዕራብ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር እና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ አባል ማስረሻ በላቸው ናቸው።
ደብረ ብርሃን ለመላው ሀገራችን ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ የሚደረገውን ሽግግር ማሳያ እና ማስወንጨፊያ ማዕከል እየኾነች ነው ብለዋል።
ይህ ውጤት የመጣው አልጋ በአልጋ ሳይኾን በብዙ ተግዳሮት ውስጥ በማለፍ መንግሥት ለልማት በሰጠው ልዩ ትኩረት መኾኑንም አንስተዋል።
ዘጋቢ፡- ሰለሞን አሰፌ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
