በኢትዮጵያ በላፉት 24 ሰዓታት ተጨማሪ 186 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፤ የሦስት ሰዎች ሕይወትም አልፏል፤ 74 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል፡፡

98

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 17/2012 ዓ.ም (አብመድ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ4 ሺህ 34 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በ186 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ እንደ ሚኒስቴሩ መረጃ አዲስ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ከስድስት ወር እስከ 75 ዓመት የዕድሜ ክልል የሚገኙ 113 ሴቶችና 73 ወንዶች ናቸው፡፡

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 147 ከአዲስ አበባ ናቸው፤ ቀሪዎቹ ደግሞ ከሶማሌ (16)፣ አፋር (10)፣ ከድሬዳዋ መስተዳድር (8)፣ ከኦሮሚያ (4) እና ከደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች (1) ክልሎች ናቸው፡፡

በ24 ሰዓቱ ከተደረገ 35 ከአስከሬን የተወሰደ ናሙና ምርመራም ከጤና ተቋም ከተወሰደ ሁለት ናሙና ቫይረሱ እንደተገኘ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ሦስት ሰዎች በቫይረሱ መሞታቸው መረጋገጡን ተከትሎ የሟቾች ቁጥር 78 ደርሷል፡፡

ትናንት 74 ሰዎች ከቫይረሱ እንዳገገሙም ተነግሯል፤ ይህንንም ተከትሎ አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 486 ደርሷል፡፡

ኢትዮጵያ እስከ ዛሬ ለ227 ሺህ 375 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ አድርጋለች፤ በዚህም በ5 ሺህ 34 ሰዎች ላይ ቫይረሱ እንደተገኘ ተረጋግጧል፤ 3 ሺህ 468 ሰዎች ደግሞ በሕክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleየአብቁተ ባንክ የመሆን ጥያቄ በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ፈቃድ ያገኛል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ዋና ሥራ አስፈጻሚው አስታወቁ፡፡
Next articleኤጀንሲው ለኮሮናቫይረስ ቅድመ መለያ የሚረዳ የተቀናጀ የሙቀት መለኪያ መሳሪያ ተግባራዊ ማድረጉን ገለጸ፡፡