
ፍኖተ ሰላም: ታኅሳስ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎጃም ዞን ”በመደመር መንግስት እይታ፤ የዘርፎች እምርታ” በሚል መሪ መልዕክት ሲሰጥ የነበረው የመካከለኛ መሪዎች ስልጠና ተጠናቅቋል።
አስተያየታቸውን ለአሚኮ የሰጡ ሰልጣኝ መሪዎች ስልጠናው በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን እንዲለዩ ያደረገ መኾኑን ገልፀዋል።
በተለይ በኢንዱስትሪ፣ በግብርና ፣ በሥራ እድል ፈጠራ እና ሌሎች ዘርፎች ላይ ያሉ እምቅ ሃብቶችን ለመለየት እና ለመጠቀም መነሳሳት እንደፈጠረላቸውም ጠቁመዋል።
ለዘርፎች የነበረውን እይታ በማሻሻል ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት በመስጠት ለልማት እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
የተሻሻሉ አሠራሮችን በመከተል የሚስተዋለውን የሥራ ዕድል ፈጠራ ችግር ለመቅረፍ እና ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ርብርብ እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል።
ዞኑ በግብርናው ዘርፍ በርካታ አቅም ያለው ቢኾንም እስካሁን ከተለመደው አሠራር ባለመወጣቱ ለውጥ ማምጣት አለመቻሉንም መሪዎች አንስተዋል።
ቀጣይ ዘመናዊ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ ለሚደረገው የገጠር ትራንስፎርሜሽን ትግበራ እንደሚተጉም አረጋግጠዋል።
በብልጽግና ፓርቲ የምዕራብ ጎጃም ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዓባይ ዓለሙ ስልጠናው መሪዎች በዘርፎች ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመፍታት ሚናቸውን እንዲወጡ የሚያስችል መኾኑን ገልጸዋል።
በተለያዩ ዘርፎች ላይ ያሉ ያሉ ዕድሎችን እና ፈተናዎችን በመለየት የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት መትጋት እንደሚገባም ተናግረዋል።
በዞኑ ለልማት ሥራዎች እንቅፋት ኾነው የቆዩ ችግሮችን ለመቅረፍ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መኾኑንም አስገንዝበዋል
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
