የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ከፌደራል እና ከክልል ከፍተኛ መሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው።

13
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የክልል እና የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ መሪዎች “የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች” በሚል መሪ መልዕክት በወቅታዊ ክልላዊ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ በደሴ ከተማ ከልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እያደረጉ ነው።
የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ሽዊት ሻንካ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አወሉ አብዲ፣ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍስሀ ደሳለኝ፣ የከተማ አሥተዳደሩ እና የዞኑ መሪዎች በመድረኩ ተገኝተዋል።
የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ተወካዮች በውይይቱ እየተሳተፉ ነው።
ዘጋቢ፦ አሚናዳብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየማኅበረሰብን ደኅንነት ለመጠበቅ የሴቶችን ጥቃት በትብብር መከላከል ይገባል።
Next article‎‎”የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች” ሕዝባዊ የውይይት መድረክ በአርባ ምንጭ እየተካሄደ ነው።